Terug naar huis, dankzij vrijwillige terugkeer.
Fedasil organiseert en betaalt uw terugreis. En we bekijken samen met u of we u nog extra steun kunnen geven.
ANY QUESTIONS? WE CAN ANSWER THEM!
-
በፈቃደኝነት መመለስ ምንድነው?
ወደ ትውልድ አገርዎ መመለስ ማለት ነው። እናም የመልቀቅ ውሳኔውን የሚወስኑት እርስዎ ነዎት። ጉዞው ከመደበኛ ተሳፋሪዎች ጋር ተመሳሳይ ነው። ባለስልጣናቶቹ ከመድረስዎ በፊት እንዲያውቁ አይደረግም። እርስዎ ላለመልቀቅ ለመወሰን ሁልጊዜም ነጻ ነዎት።
-
በፈቃደኝነት ለመመለስ እንዴት ማመልከት እችላለሁ?
ቤልጅየም ውስጥ ካሉ የመመለሻ ጠረጴዛዎች ወይም ድርጅቶች አንዱን ያነጋግሩ፣ የማህበራዊ ጉዳይ ሰራተኛዎን ያነጋግሩ ወይም በነጻ የስልክ ቁጥር 0800 327 45 ይደውሉ።
-
መመለሴን ማን ያደራጃል?
Fedasil (ጥገኝነት ጠያቂዎችን የመቀበል ፌዴራል ኤጀንሲ) በፈቃደኝነት የመመለስ መርሃ ግብር ተጠያቂ ነው። Fedasil ወይም አለምአቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) የበረራ ወይም የአውቶቡስ ጉዞዎን ያደራጃል። ከመጡ በኋላ IOM እና Caritas International (ዓለም አቀፍ የምግብ እና የእርዳታ ድርጅት ነው) እርዳታ ይሰጣሉ።
-
መክፈል ያስፈልገኛል?
አይ፣ መክፈል የለብዎትም። Fedasil ለአውሮፕላን ወይም ለአውቶቡስ ትኬት እንዲሁም ወደ አውሮፕላን ማረፊያ ወይም ወደ ጣቢያው ለሚደረግ ጉዞ ይከፍላል። ከቆንስላ ቢሮዎች የራስዎን የጉዞ ሰነድ መውሰድ ያለብዎ ሲሆን ሊለቁ ሲሉ ለዚህ ያወጡት ገንዘብ ተመላሽ ይደረግልዎታል።
-
ከእኔ ጋር ምን ያህል ሻንጣ መያዝ እችላለሁ?
የአየር መንገድን ወይም የአውቶቡስ ኩባንያዎችን የሻንጣ ገደብ ማክበር አለብዎት፤ ለአንድ ሰው የሚፈቀደውን የሻንጣዎች ብዛት ወይም ከፍተኛ ክብደት አይለፉ። ስለዚህ እራስዎን መገደብ አለብዎት!
-
በመመለሴ ጊዜ እርዳታ አገኛለሁ?
አዎ፣ ከቤልጂየም ሲወጡ የIOM ወይም የFedasil ሰራተኛ የአውሮፕላን ትኬቶችን እና ምናልባትም አበል ይሰጥዎታል። ሰራተኛው ወደ ድንበር ቁጥጥር አብሮዎት ይሄዳል። የIOM ወይም የFedasil ሰራተኛ በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ ወደ ኤርፖርት መውሰድ ያለብዎት ሊታወቅ የሚችል ቦርሳ ያገኛሉ። ከፈለጉ እና ከተቻለ የIOM ወይም የFedasil ሰራተኛ በትውልድ ሀገርዎ አየር ማረፊያ ሊጠብቁዎት ይችላሉ።
-
በአገሬ ውስጥ ኑሮ ቀላል አይደለም እናም ምን አይነት ድጋፍ ልታቀርቡ ትችላላችሁ?
እርስዎን በመልሶ መቀላቀል ጉዞዎ ሊረዱ ከሚችሉ በትውልድ አገርዎ ውስጥ ከሚገኙ አጋር አካላት ጋር በትብብር እንሰራለን። ይህ ምናልባት የእርስዎን የጤና ወጪዎች መሸፈንን፣ ስራዎን መደገፍ፣ የራስዎን የንግድ ሥራ መጀመርን ሊያካትት ይችላል። ይህ እርዳታ ለሁሉም ሰው የሚሰጥ አይደለም፣ እያንዳንዱ ጉዳይ የተለየ ነው። የትኛው አይነት እርዳታ ማግኘት እንደሚችሉ ለማወቅ እባክዎን ተጠሪዎን ያነጋግሩ። እንዲሁም ከመልቀቅዎ በፊት የተመላሾች ተቆራጭ ይሰጣል።